From Defeating Colonialism to Facing Genocide: Historical Precedents and Prospects of the Amhara Existential Struggle in Ethiopia
Main Article Content
Abstract
This research examines the Amhara people’s existential struggle in Ethiopia by analyzing the historical, political, and ideological factors that marginalize them. It employs Historical Analysis (HA) and Foucauldian Discourse Analysis (FDA) to critique false historical narratives, ethnonationalist rhetoric, and assimilationist agendas that portray the Amhara as oppressors, fueling ethnic politics, hate speech, and targeted attacks. The rise of the Fano movement is explored as a grassroots response that reflects Amhara resilience. Three key factors—colonial conspiracy, ethnonationalist vengeance, and Oromummaa’s assimilationist agenda—have fostered division, demonized Amhara identity, and eroded their cultural and political presence. Despite internal divisions within Fano regarding the strategic role of Amhara nationalism, its resurgence signifies a growing commitment to preserving Amhara identity and countering existential threats. The study underscores the need to redefine Amhara nationalism to include linguistic and cultural affiliations while retaining core values. Recommendations include preserving Fano as a public identity, unifying its leadership, and integrating Ethiopianist principles to create a balanced, inclusive approach.
አጠቃሎ
ይህ ጥናት የዐምሐራ ሕዝብን ለህልውና አደጋ የዳረጉ ዐበይት መንስኤዎችን እና የህልውና ተጋድሎውን ሂደት ይቃኛል። የጥናቱ ስልት የታሪክ እና የትርክት ትንተና ሲሆን ስሁት የታሪክ ትርክቶች፥ ዐምሐራ-ጠል ብሔርተኝነት እና የባህል ስረ-መሠረት ያላቸው ሰልቃጭ-የፖለቲካ ፍላጎቶች፡ ዐምሐራን በማንነቱ ኢላማ አድርገው ሊያጠፉት የተነሱ አጀንዳዎች መሆናቸው ተለይቷል። የሀሰት ትርክቶች መጀመሪያ የተጠነሰሱት ቅኝ ግዛት ባልተሳካላቸው አካላት፡ ሀገሪቱን በውስጥ ኃይሎች ለማፈራረስ ሲሆን፡ እያደር ግን በሀገር ውስጥ የተፈለፈሉት ዐምሐራ-ጠል ጽንፈኛ የብሔር ፖለቲከኞች ፋሽን ያደረጉት ሴራ ሁኗል። የሀሰት ትርክቶቹ በዋናነት፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ዐምሐራ ሌሎቹን ማህበረሰቦች ጨቋኝና በዝባዥ ሕዝብ እንደነበረ የሚገልጹ ሲሆን፡ አላማቸውም “ዐምሐራ በድሎናልና እንበቀለዋለን” ለሚሉ ኃይሎች ማስተባበያ መሆን ነው። እነዚህ የሀሰት ትርክቶች በተሳካ ሁኔታ ዐምሐራ-ጠልነትን እና የ“በቀል” ስሜትን መፍጠር ችለዋል። አሁን በዐምሐራ ላይ ለሚሰነዘሩ የጥላቻ ንግግሮች እና እየተፈጸመ ላለው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ምክንያት ተደርገው የሚነሱት እነዚህ የሀሰት ትርክቶችና የሴራ ክሶች ናቸው። ከዚህ ጎን ለጎን፡ በዐምሐራ ላይ የሚፈጸምን የተቀናጀ ጥቃት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ሰልቃጭ ማንነቱን እና የባህል የበላይነቱን ለማስፈን እየሰራ ያለ የፖለቲካ ኃይልም አለ። ይህ ኃይል የህዳጣንን ማንነትና እሴቶች አጥፍቶ የራሱን ማንነት በመጫን አጎራባች ማኅበረሰቦችን መዋጥ የለመደ ባህል አለው። ሀገሪቱን በሙሉ ለመዋጥ በሚያደርገው ዘመቻ በቀላሉ አይዋጠኝም ወይም ያንቀኛል ብሎ የለየው የዐምሐራን ማኅበረሰብ ማንነትና እሴት ነው። ስለዚህ ይህ ኃይል ከውጭም ሆነ ከውስጥ በመነጩ ጸረ-ዐምሐራ ትርክቶች ተጠቃሚና ጸረ-ዐምሐራ አሰላለፍ ካላቸው አካላት ጋር ሁሉ የሚቀናጅ ነው። አላማው በቡድንም ሆነ በግል ተጋጥሞ ዐምሐራን ማዳከም (ማጥፋት) እና ዘለዓለማዊ የሆነ የባህል፥ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነትን መያዝ ነው። ይህን የህልውና አደጋ በመገንዘብ ለትጥቅ ትግል የተነሳው የፋኖ ኃይል፡ ዘርፈ-ብዙ ውስጣዊ መተጋገሎችንም እያደረገ መሆኑ ተስተውሏል። በተለይ በዐምሐራ ብሔርተኝነት እና በህልውና ተጋድሎው ማዕቀፍ ላይ የጠራ አገነዛዘብና አንድ ዓይነት አሰላለፍ ለመፍጠር እየተሠራ ነው። ዐምሐራነትና ኢትዮጵያዊነት የማይምታቱ ማንነቶች መሆናቸውን በመገንዘብ የፋኖን ሚና በግልጽ ማስቀመጥ ይመከራል። ፋኖን የግል ሠራዊታቸው አድርገው የሚመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችና አደረጃጀቶች ሕዝቡን ወደ ባርነት እንጂ ወደ ነጻነት ስለማይወስዱት፡ ፋኖ ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ርእዮተ ዓለም የጸዳ፡ የሁሉም ዐምሐራ-ተኮር ፖለቲካዊ እሳቤዎችና አደረጃጀቶች የጋራ ቤት (ማኅበራዊ መሠረት) የሚሆን፡ የሕዝብ ቅርስና ማንነት እንዲደረግ ይህ ጥናት ያሳስባል። ፋኖን የግል ሰራዊቱ አድርጎ የሚፈጠር ፓርቲን በምርጫ ከስልጣን ማውረድ አይቻልምና፡ የዐምሐራ ትግል ጠላቱን ብቻ ሳይሆን መሪዎቹንም መመርመር ይገባዋል።
Article Details

This work is licensed under a Creative Commons Attribution-NonCommercial-NoDerivatives 4.0 International License.