Semantic Changes of the Amharic verb አለ alə ‘say’ Its Lexicalization and Grammaticalization Routes
Main Article Content
Abstract
This study argues for two claims; 1) treating the three forms of the Amharic verb አለ ‘say’ –አል al ‘AUX’, and –አል–al ‘INFLECTION’ as etymologically the same and 2) describing meaning extensions of the Amharic verb al ‘say’ from being a verb of communication evolving to that of reporting, mean, understand, call, hit, ignore, causal, purposive, confirmation, negation, invite or forbid to speak, auxiliary, valency changer (intransitive), modal auxiliary, verbalizer, expressive and tense-aspect-modal marker. These meaning extensions happened through the two language change processes, lexicalization and grammaticalization. The 33 sets of data for the analysis and discussion come from various written sources and introspective data from the author. To discuss meaning extensions of ale ‘to say’ two descriptive semantic change models Bybee and Dahl (1989) and Heine and Kuteva (2002, 2005) have been used.
አጠቃሎ
ይህ “የዐማርኛ “አለ” ግስ ቃላዊና ሰዋስዋዊ የፍቺ ለውጦች” የተሰኘ የጥናት ጽሑፍ ኹለት ግቦች አሉት። አንደኛው በዐማርኛ የግስ መዋቅር በተለያየ ዐውድ የሚከሰቱ ሦስቱን “አለ” ምዕላዶች "ሥርወ-ቃላቸው” አንድ መኾኑን ማሳየት እና ኹለተኛው የዐማርኛ “አለ” ግስ ፍቺ ለውጦችን ከንግግር ግስነት ወደ ራፖር አቅራቢ፣ ፍቺ፣ መረዳት፣ መባል፣ መምታት፣ ችላ ማለት፣ ሰበብ፣ ዓላማ፣ ማረጋገጫ፣ አሉታዊ፣ የ(አለ)መናገር ግብዣ፣ የግስ ረዳት፣ ማሟያ ስም ጨማሪነት፣ ኹኔታዊ ረዳት ግስነት፣ ግስ አድራጊነት፣ ቃል አካይነት፣ እና ወደ ጊዜና አንቀፅ አመልካችነት ማደጉን ማሳየት ነው። ይህ ጥናት አትኩሮቱ በዐማርኛ እነዚህ የ“አለ” የፍቺ አንድምታዎች ቃላዊ እና ሰዋስዋዊ የለውጥ መንገድ የተከሉትን ብቻ ነው። በዚህ መጣጥፍ እነዚህን ቃላዊ እና ሰውስዋዊ ፍቺያዊ ለውጦች ለማስረዳት ከጸሐፊውና ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ 33 የቋንቋው አስረጅዎች ጥቅም ላይ ውለዋል። የ“አለ”ን ቃላዊና ሰዋስዋዊ ለውጦችን ለመወያየት ይህ ጥናት የባይቢና ዳል (1989) እንዲሁም የሃይነና ኩቴቫ (2002, 2005) ሞዴሎችን መሠረት አድርጓል።
Article Details

This work is licensed under a Creative Commons Attribution-NonCommercial-ShareAlike 4.0 International License.