December 20, 2024

Call for Papers

07 October 2024

To whom it may concern

Subject: Call for papers

We cordially invite you to submit your research manuscripts for publication in the upcoming inaugural issue of the Journal of Amhara studies (JAS). JAS is an open access, quarterly, multidisciplinary journal that publishes articles in Amharic and English. The journal’s aim is to provide a platform for the dissemination of research and critical thought on issues affecting the Amhara people, Ethiopia, and the wider region. We invite submissions from academics, policymakers, and the public who would like to contribute to knowledge in our key focus areas.

Topics of Interest for the Journal are Economics, Development, and Rehabilitation; Science and Technology; Health, Education, and Social Services; Agriculture, Environment, and Climate Change; Politics and Human Rights; Amhara Culture and Language; History; and Internal, Regional, and International Relations. We encourage authors to primarily focus on matters that the Amhara people find themselves in currently, for the inaugural issue.

Manuscripts may be submitted through submissions@journalofamharastudies.org. For detailed guidelines on formatting, manuscript submission, and other relevant information, please visit our website at https://journalofamharastudies.org.

We will take this opportunity to request for the dissemination of this letter widely.

Sincerely,

Girma Berhanu, Professor

Editor-in-Chief,

Journal of Amhara Studies, JAS

መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.

ለሚመለከተው ሁሉ፤

ጉዳዩ፤ ጥናታዊ ጽሁፎችን ስለመጋበዝ

በመጀመሪያው የዐማራ ጥናት መጽሔት (JAS) ሊታተሙ የሚችሉ ጥናታዊ ጽሁፎችን መቀበል መጀመራችንን ስናበስር እና አጥኚዎች ጽሁፎቻችሁን እንድትልኩልን ስንጋብዝ ከልብ በመነጨ ደስታ ነው። በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የሚታተመው የዐማራ ጥናት መጽሔት በነጻ የሚሰራጭ፣ በዓመት አራት ጊዜ የሚታተም፣ የጥናት ዘርፎች መድብል ነው።  የዐማራ ጥናት መጽሔት፤ የዐማራን ሕዝብ፣ ኢትዮጵያን እና ባጠቃላይም ቀጣናውን የተመለከቱ የረቀቁ የጥናት ውጤቶችን እና ጥልቀት ያላቸውን ትንታኔዎች ማቅረብን ያለመ መድረክ ነው። ከታች በተመለከቱት የአትኩሮት ዘርፎች ላይ ጽሁፍ ማቅረብ የትምችሉ በከፍተኛ ትምህርት እና በምርምር ተቋማት የምትገኙ ተመራማሪዎችን፣ ፖሊሲ አውጭዎችን እና ማኅበረሰባችንን በተለያዩ ዘርፎች እያገለገላችሁ የምትገኙ ምሁራን ጽሁፎቻችሁን እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል።

የዐማራ ጥናት መጽሔት የትኩረት ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው፤ ምጣኔ ሀብት፣ ልማት እና መልሶ ማቋቋም፤ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፤ ጤና፣ ትምህርት እና ማኅበራዊ አገልግሎቶች፤ ግብርና፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ፤ ፖለቲካ እና ሰብዓዊ መብት ነክ ጉዳዮች፣ የዐማራ ባህል እና ስነ ቋንቋ፤ ታሪክ፤ እና ውስጣዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም-አቀፋዊ ግንኙነቶች። በተለይም፤ በመጀመሪያው እትም፤ የዐማራ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት ያለበትን ሁኔታ የሚመለከቱ ጥናታዊ ጽሁፎችን  የመጽሔቱ አስተዳደር ያበረታታል።

ጥናታዊ ጽሁፎች በኢሜይል አድራሻችን፤ submissions@journalofamharastudies.org፤ ሊላኩ ይችላሉ።የጽሁፎችን ቅንብሮች፣ አላላክ እና ሌሎች ተዛማጅ ዝርዝር መረጃዎች ለማግኘት በ https://journalofamharastudies.org የሚገኘውን የበይነ-መረብ ገጻችንን መጎብኘት ይቻላል።

በዚህ አጋጣሚ፤ ይህንን ደብዳቤ በሰፊው በማሰራጨት እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።

ከአክብሮት ጋር፤

ግርማ ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)

ዋና አርታዒ፤

የዐማራ ጥናት መጽሔት።